የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
ጥቅምት 01 2017 ዓ.ም
- “በአፍሪካ ውስጥ የተዛባ መረጃን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን መከላከል፡ ተግዳሮቶች፣ ፈጠራዎች እና ስትራቴጂካዊ ምላሽ” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ መረጃ ማጣራት ጉባዔ በጋና አክራ ከተማ ተካሄደ። በጉባዔው ከ30 በላይ የአፍሪካ አገሮች የተወጣጡ 50 የመረጃ አጣሪ ተቋማት ተሳትፈውበታል። ኢትዮጵያ ቼክም በጉባዔው ተገኝቷል። በጉባዔው ሀሰተኛና የተዛባ መረጃዎች ሰዎች ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኙ የሚፈጥሯችው ተግዳሮቶች ለመቀነስ የህዝብ በሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት ግንዛቤ ማሳደግ፣ የመረጃ ማጣራት ሂደቶችና አቅም ማጎልበት፣ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ለመቀነስ ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር መተባበር የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል። እንደ እአአ ከጥቅምት 9 – 10 ቀን 2024 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የተካሄደውን ጉባዔ ያሰናዳው አፍሪካ ቼክ (Africa Check)፣ ከፋክት ስፔስ ዌስት አፍሪካ እና ከዱባዋ አምፕሊፋይንግ ትሩዝ ጋር በመተባበር ነበር።
- ቲክቶክ በርካታ የይዘት አስተናባሪ ሠራተኞቹን (Content Moderators) በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ሊተካ መሆኑን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት አስነብቧል። ሰዎችን በቴክኖሎጅ በመተካት ሂደቱም ከ500 በላይ ሠራተኞች እንደሚቀነሱ ተገልጿል። የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት አስተናባሪ ሰዎችን በሰውሰራሽ አስተውሎት የመተካት እንቅስቃሴው ሀሠተኛ መረጃዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን ከአውድ አንጻር የመረዳት ክፍተትን ይፈጥላ የሚሉ ድምጾች በብዛት እንደሚደመጡ ይታወቃል።
- ብራዚል በኤክስ/ትዊተር ላይ ጥላው የነበረው እግድ ማንሳቷን አለም አቀፍ ሚዲያዎች በሳምንቱ አጋማሽ ዘግበዋል። የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕግዱ ያነሳው ኤክስ የ5.1 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት መክፈሉን ተከትሎ ሲሆን በተጨማሪም ሀሠተኛ መረጃ ያሰራጫሉ የተባሉ በርካታ አካውንቶችን መዝጋቱንና የሀገሪቱ ዜጋ የሆነ ቋሚ ተወካይ መቅጠሩ ተገልጿል። ኤክስ እአአ በ2022 ብራዚል በተደረገው ምርጫ ሀሠተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የተባሉ አካውንቶችን እንዲዘጋ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ትዕዛዝ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ዕግድ ተጥሎበት እንደነበር ይታወቃል።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-በቀድሞዋ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ላይ የቀረበን አነጋጋሪ ፅሁፍ የተመለከተ መረጃ አቅርበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2470
-የጥላቻ መልዕክት የሚያደርሰውን ጉዳት የሚያስቃኝ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2471
-የሞቱ ወታደሮች በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚያሳይ ቪዲዮን አጣርተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2472
-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨ መረጃም ፈትሸናል: https://t.me/ethiopiacheck/2474
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::