የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
መስከረም 24፣ 2017 ዓ.ም
- ግዙፉ የቴክኖሎጅ ኩባንያ ሜታ በቀላሉ ቪዲዮና ድምጽ መስራት የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት መገለገያን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ይህ ሙቪ ጄን (Movie Gen) የሚል ስያሜ የተሰጠው መገልገያ በጽሁፍ የቀረበን ሀሳብ በፍጥነት ወደ ተንቀሳቃሽ ምስል መቀየር የሚችል ሲሆን ማጀቢያ ሙዚቃና ድምጽም ማምረት ይችላል ተብሏል። መገልገያው ለሲኒማ ኢንዱስትሪ በእጅጉ እንደሚጠቅም የተነገረ ቢሆንም ለሀሠተኛ መረጃ ስርጭት የመዋል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የተመለከቱ አስተያየቶችም በመሰጠት ላይ ናቸው።
- በመጭው ታህሳስ በጋና የሚደረገው ምርጫ በሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ተጽኖ ስር እናዳይወድቅ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ሀላፊነት አለባችሁ ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት አሳስበዋል። በ28ኛው የጋና ጋዜጠኞች ዓመታዊ የሽልማት መርሐግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት አኩፎ-አዶ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ በዴሞክራሲ ምርጫ ስርዐት ላይ የደቀነውን ስጋት አስታውሰው ጋዜጠኞች “የዕውነት ዘብ” እንዲሆኑ መክረዋል።
- ሜታ በማህበራዊ ፕላትፎርሞቹ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ ከባንኮች ጋር በሙከራ ደረጃ የጀመረው መረጃ የመለዋወጥ አሰራር ውጤት እንዳመጣለት በሳምንቱ አጋማሽ ባስነበበው መግለጫ አስታውቋል። ካምፓኒው የሙከራ አሰራሩን ከስድስት ወራት በፊት በዩኬ ከሚገኙ ባንኮች ጋር መጀመሩን ገልጾ በዚህም በማጭበርበር ድርጊት ላይ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ከ20,000 በላይ አካውንቶችን ማስወገድ መቻሉን አብራርቷል። በሜታ ስር የሚተዳደሩት ፌስቡክና ዋትስአፕ የማጭበርበር ድርጊት በስፋት ከሚፈጸምባቸው የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ከቀዳሚዎቹ እንደሚመደቡ ጥናቶች ያሳያሉ።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የተፈበረኩ ምስሎች የፈጠሩትን ስጋት የሚዳስስ ጽሁፍ አቅርበናል:https://t.me/ethiopiacheck/2462
-የግብጽ ሚዲያዎች በታላቁ የሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በማለት ያሰራጩትን መረጃ ፈትሸናል:https://t.me/ethiopiacheck/2463
-በአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ የተሰራጨን ሀሠተኛ መረጃ አጣርተናል:https://t.me/ethiopiacheck/2464
-ተመሳስለው የሚከፈቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚረዱ ነጥቦችን አቅርበናል:https://t.me/ethiopiacheck/2465
-ታዋቂውን ሲኒማቶግራፈርና ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማውን (ሶሚክ) ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ ሀሠተኛ የፌስቡክ አካውንት ያሰራጨውን የማጭበርበር ድርጊት አጋልጠናል:https://t.me/ethiopiacheck/2466
-ከቪዲዮ ጌም ተወስዶ የተጋራን ቪድዮም ፈትሸናል:https://t.me/ethiopiacheck/2467
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::