የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህይወታቸው አልፏል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህይወታቸው አልፏል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ነሀሴ 25፣ 2017

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህይወታቸው አልፏል በሚል በሀገራችን እና በውጪ ማህበራዊ ሚድያ እና በሚድያዎች እየተሰራጩ ያለ መረጃዎች እንዳሉ ተመልክተናል።

መረጃው በአንዳንድ የአሜሪካ ሚድያዎች ጭምር ሽፋን ያገኘ ሲሆን ጥቂት የማይባሉ የሀገሪቱ ፖለቲከኞችም ትኩረት ሰጥተውት እየተነጋገሩበት ይገኛሉ።

‘ዶናልድ ትራምፕ ሞተዋል’ አልያም ‘ከእይታ ጠፍተዋል’ የሚሉ ፅሁፎች በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች፣ በዋነኝነት ደግሞ ኤክስ (X) ላይ እየተለጠፉ እና እየተጋሩ የታዩ ሲሆን እነዚህን ፅሁፎች ከለጠፉ የኤክስ አካውንቶች መሀል ‘Trump Tracker’ የተባለ ከ32 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አካውንት ይገኝበታል።

ይህ አካውንት ትራምፕ መሞታቸውን አልያም በጠና ታመው ከእይታ መጥፋታቸውን የሚጠቁም ፅሁፍ አጋርቷል።

በተመሳሳይ ‘CaraMia 200’ የተባለ 12,939 ተከታዮች ያለው የኤክስ አካውንት የትረምፕ የጤና ሁኔታን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ‘#WhereIsTrump እና #TrumpHealth የሚሉ ሃሽታጎችን በመጠቀም ትራምፕ በጠና መታመማቸውን የሚጠቁም ፅሁፍ አጋርቷል።

የ79 አመቱ ትራምፕ ከጤናቸው ጋር በተያያዘ እጃቸው ላይ ያጋጠማቸውን ህመም እንደ BBC እና CNN የመሳሰሉ አለም አቀፍ ታዋቂ ሚዲያዎች በቅርብ ወራት ዘገባ ሰርተው ነበር: https://edition.cnn.com/2025/07/17/politics/trump-leg-swelling-chronic-venous-insufficiency, https://www.bbc.com/news/articles/c1jw1pdyp0jo

ከዚህ ባለፈ ግን ታዋቂ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ትራምፕ በጠና መታመማቸውን አልያም ህይወታቸው ማለፉን የሚገልፅ ዘገባዎች በቅርብ ቀን አልሰሩም።

በተቃራኒው CNN ትራምፕ ቅዳሜ የጎልፍ ስፖርት ሲጫወቱ እንደዋሉ ዘግቧል: https://edition.cnn.com/2025/08/30/politics/where-is-donald-trump

ለሪፐብሊካን ፓርቲ ቅርብ እንደሆነ የሚነገርለት ‘New York Post’ በተመሳሳይ የተሰሬጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በመጥቀስ መረጃ አስነብቧል: https://nypost.com/2025/08/30/us-news/president-trump-is-alive-and-well-after-online-rumors-of-his-death/

ማህበራዊ ሚድያ ላይ እንዲሁም በአንዳንድ ተዓማኒነት በጎደላቸው ሚድያዎች ላይ የሚሰራጩ ምንጫቸው የማይታወቅ መረጃዎችን ተቀብለን ከማሰራጨት በመቆጠብ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::