የደብረ ብርሃን ከንቲባ “ተገደሉ” ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው

ነሐሴ 19፣ 2015 ዓ.ም
ከ6 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትን እና Quohii Post የሚል መጠሪያ ያለው የፌስቡክ ገጽ የደብረ ብርሃን ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደተገደሉ የሚገልፅ መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል።
ይህ መረጃ ከላይ ከተጠቀሰው የፌስቡክ ገጽ በተጨማሪ በምስሉ ላይ እንደሚታየው በሌሎች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በስፋት መጋራቱንም አስተውለናል።
ኢትዮጵያ ቼክ መረጃው ሀሠተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን የደብረ ብርሃን ከንቲባ የሆኑትን አቶ በድሉ ውብሸትንም በስልክ አነጋግሯል።
አቶ በድሉ ስለተሰራጨው መረጃ መስማታቸውን ገልጸው “አለሁ፣ ይወራል እንግዲህ ምን ማድረግ እንችላለን!” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
ከንቲባው መገደላቸው የሚገልጹ ሀሠተኛ መረጃዎች ከመሰራጨታቸው ቀደም ብሎ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚቀሰቅሱና የሚያበረታቱ ይዘቶች በስፋት ሲሰራጩ እንደነበርም ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።
ምንጫቸው ከማይታወቅ እና ካልተረጋገጡ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
