በአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው
መስከረም 20፣ 2017 ዓ.ም
‘Yehabesha’ የተባለው እና ከ1.9 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት ገፅን ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህይወቱ እንዳለፈ ዛሬ መረጃ ሲያጋሩ ውለዋል።
እነዚህ ፅሁፎች ምንም አይነት ምንጭ ሳይጠቀስባቸው ለህዝብ የተጋሩ ሲሆን በርካታ ሰዎችም መልሰው ሲያጋሩት (ሼር ሲያደርጉት ተመልክተናል)፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ፅሁፉን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።
የመረጃ ማጣርያ ዴስካችን በዚህ ዙርያ አንድ የአርቲስቱ ጓደኛን እና አንድ የቅርብ ቤተሰብን ያነጋገረ ሲሆን በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገረዋል።
“እኛም ከመሸ አይተነው ነበር፣ በርካታ ሰው ተደናግጦ ሲደውል ነበር፣ ወሬው ግን ውሸት ነው። ከእንዲህ አይነት በሬ ወለደ ፅሁፍ ምን እንደሚጠቀሙ አይገባኝም” ብለው ምላሽ የሰጡን ምንጫችን ይህ በአርቲስቱ ዙርያ ሲወራ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን ትክክለኛነት ሳናጣራ፣ የምናምናቸው ምንጮች ሳይዘግቡት እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳንመለከት ባለማመን እና መልሰን ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::