ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ “ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ “ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ግንቦት  28፣ 2016

የዘንድሮው የኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ በሁለቱ የደቡብ ኮሪያ ከተሞች ሴኡል እና ኢልሳን እየተካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በጉባዔው በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጉባዔው ተሳትፎ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ሲሆን ከነዚህ መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው “ብቸኛውና ተጠባቂው አፍሪካዊ ተናጋሪ” እንደሆኑ የሚገልጽ መረጃ አንዱ ነው።

ይህን መረጃ ካጋሩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከልም Ethio info Center፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አርበኞች እና Gibe Media /GM/ የተሰኙ የፌስቡክ ገጾች ይገኙበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በጉባዔው ‘ብቸኛው አፍሪካዊ ተናጋሪ’ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች በመድረኩ ንግግር አድርገዋል።

ከነዚህ መካከል የርዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አንዱ ሲሆኑ ፕሬዝዳንቱም አፍሪካና ኮሪያ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ሮቦቲክስ እንዲሁም አነስተኛ የኑክሌር ማብላያዎች ዘርፍ አብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በቪድዮ የተደገፈው የርዋነዳው ፕሬዝዳንት ንግግርም በተረጋገጠው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኤከሰ (X) አካዉንት ተጋረቷል፡ https://x.com/urugwirovillage/status/1797911676794388730?s=48&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶም በኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ግብርና፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ሰላምና ጸጥታ ኮሪያና አፍሪካ በትብብር እንዲሰሩባቸው ያነሷቸው ጉዳዮች ናቸው።

ይህ ንግግርም በፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ‘X’ አካውንት ላይ ተለጠፏል፡ https://x.com/williamsruto/status/1797998068388045023?s=48&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

በሌላ በኩል የመጀመሪያው በሆነው የ2024 የኮሪያ-አፍሪካ ጉባዔ 48 የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን የ25 አፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጉባዔው መገኘታቸው ተዘግቧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::