የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ- ኀዳር 13፣ 2017
ኀዳር 13፣ 2017
- ከወር በኃላ በጋና በሚደረገው ምርጫ ዋዜማ በተቀናጀ ሁኔታ የገዥው ፓርቲን ዕጩ የሚደግፉ እና ተቃዋሚዎችን የሚያንኳስሱ 171 ቦት የኤክስ የትዊተር አካውንቶችን ማግኘቱን ኒውስጋርድ የተባለ የድረገጾች ተከታታይ ተቋም አስታውቋል። ተገኙ የተባሉት ቦት የኤክስ አካውንቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክንሎጂ የሚመረቱ ምስሎችን ለፕሮፋይላቸው ይጠቀማሉ የተባለ ሲሆን የሚያጋሩት ጽሁፍም በቻትጅፒቲ (ChatGPT) አማካኝነት ይጻፍ ነበር ተብሏል።
- ሜታ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ በማጭበርበር ድርጊት ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ከ2 ሚሊዮን በላይ አካውንቶችን ከፕላትፎርሞቹ ማጽዳቱን በትናትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ላጤ፣ የመንግስት ኤጀንሲ ወይም ሌላ አይነት የሚታመን ማንነት በመጠቀም፤ አጓጊ የስራ ዕድል በማቅረብ በሰዎች ላይ የገንዘብ ኪሳራ ያደርሱ ነበር የተባሉት አብዛኞቹ አካውንቶች በደቡብ እስያ እና በተባበሩት አርብ ኤሚሬቶች መቀመጫቸውን ባደረጉ የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች የሚዘወሩ ነበር ተብሏል።
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ዩኔስኮ እና ብራዚል ከአየር ንብረት አንጻር የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመታገል ያለመ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በሳምንቱ አጋማሽ አስታውቀዋል። በቡድን አገሮች ስብሰባ ማጠቃላያ ላይ ይፋ የሆነው ይህ ስምምነት ሀገሮች አየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚያደርጉት ምክክር አንጻር ሳንካ የሚፈጥሩና የሚያጓትቱ ሀሰተኛ መረጃዎችን በንቃት ለመዋጋት ያስችላል ተብሏል።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-የማህበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት በሚለው ጉዳይ በትግረኛ መልዕክት አስተላልፈናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2508
-የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከሰሞኑ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጭር ውጭ እየሆነ ነው” እንዳሉ ተደርጎ የተጋራን መረጃ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2509
-የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የመኪና መገጣጠሚያ ሲያስመርቁ ያሳያል ተብሎ የተጋራው ቪዲዮም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2510
-በአቶ ጃዋር መሐምድ ስም የተከፈተን ሀሠተኛ የኤክስ/ትዊተር አካውንትም አጋልጠናል: https://t.me/ethiopiacheck/2512
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::