ኢቢሲ በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አዲስ ሪፖርት ዙርያ ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ኢቢሲ በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አዲስ ሪፖርት ዙርያ ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ጥቅምት 7፣ 2018

ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2025 ከሰሀራ በታች ከሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ ዕድገት አስመዝጋቢ ሀገር እንደምትሆን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትንበያ እንዳመላከተ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በዛሬው ዕለት መረጃ አጋርቷል።

ከኢቢሲ መረጃ ጋር አብሮ የተያያዘው ምስል እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ የ7.2 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ቀዳሚዋ ሀገር ናት።

ይሁንና ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት መረጃው የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጧል።

አይ ኤም ኤፍ ትናንት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዲሁም በድረ-ገፁ ላይ ያጋራው መረጃ እንደሚያሳየው ደቡብ ሱዳን የ24.3 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚዋ ናት፣ ኢትዮጵያ እና ጊኒ ደግሞ እያንዳንዳቸው 7.2 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/1MWaNg5Gqc/)

በተጨማሪ በአለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት ትንታኔ መሰረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሞ በቀጣዩ 2026 ከሰሀራ በረሃ በታች ካሉ አፍሪካ ሃገሮች በ7.1 ፐርሰንት እድገት አራተኛውን ትልቁ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠብቃል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ ሁለተኛ ቦታን እንደያዘ ይፋ ቢደረግም አምና አስመዝግቦት ከነበረው 8.1 ፐርሰንት እድገት ወደ 7.2 ፐርሰንት አሽቆልቁሏል፣ ይህም የ0.9 ፐርሰንት መንሸራተትን ያሳያል።

አይ ኤም ኤፍ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራት አማካኝ እድገት 4.1 ፐርሰንት መሆኑን ጠቅሶ የቀጠናው ሀገራት ኢኮኖሚ መሻሻል እያሳየ መሆኑ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::