“ኢትዮጵያ ውስጥ ተይዛ ትገኛለች” በሚል ቪድዮዋ እየተሰራጨ ስለሚገኘው ሴራሊዮናዊት ጉዳይ በኢትዮጵያ የሴራሊዮን ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ቼክ የሰጠው ማብራሪያ

Does Ethiopia have a Sierra Leonean who has been "imprisoned"?

ሐምሌ 30፣ 2016 ዓ.ም

ከሰሞኑ “ኢትዮጵያ ውስጥ ባልታወቀ ቦታ ተይዛ ትገኛለች” በሚል የአንዲት ሴት ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

በግምት በጎልማሳ እድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ይህች ሴት የእስር ቤት ፍርግርግ ከሚመስል ብረት ጀርባ እርቃኗን ቆማ እያለቀሰች ስታወራ ይታያል።

ይህን ቪድዮ በተለይ በሴራሊዮን ማህበራዊ ሚድያዎች ዘንድ በስፋት ሲጋራ የሰነበተ ሲሆን ቪድዮውን ካጋሩ ድረ-ገጾች መካከል ሴየራሎድድ የተሰኘ ድረ-ገጽ ይገኝበታል፡ https://sierraloaded.sl/diaspora/embassy-ethiopia-information-disturbing-video-female-citizen/

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ በኢትዮጵያ የሴራሊዮን ኤምባሲን መረጃ የጠየቀ ሲሆን ኤምባሲው ጉዳዩን ከማህበራዊ ትስስር ገጾች መመልከቱን እንዲሁም ግለሰቧ የሀገሪቱ ዜጋ መሆኗን ሴራሊዮን ከሚገኙ ዜጎች መረጃ ማግኘቱን ለኢትዮጵያ ቼክ ገልጿል።

ቪድዮው በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ከተመለከተ በኋላ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ማናገሩን ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቧ በእነርሱ ቁጥጥር ስር እንደማትገኝ መግለጻቸውን ኤምባሲው አሳውቋል።

በተጨማሪም ቪድዮው ኢትዮጵያ በሚገኙ የሴራሊዮን ማህበረሰብ አባላት እንደተቀረጸ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተገለጸ የሚገኝ ሲሆን ኤምባሲው ግን ጉዳዩን በተመለከተ ለኤምባሲው ጥቆማ ወይም መረጃ የሰጠ ግለሰብ እንደሌለ ነግሮናል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::