በኬንያ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገበት እህልን በተመለከተ የሀሰተኛ እና ትክክለኛነታቸዉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ስርጭት መበራከቱ ተነገረ

ሰኔ 02፣ 2015
- በኬንያ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገበት በቆሎ ወደ ሀገር ማስገባት በተመለከተ የሀሰተኛ እና ትክክለኛነታቸዉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ስርጭት መበራከቱ ተነገረ። ሀገሪቱ የአፍሪካ ቀንድን ባጠቃዉ ድርቅ ምክንያት ሰው ሠራሽ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገባቸው የእህል ዘሮችን ማምረት እና ወደ ሀገር ማስገባት ላይ ለአስር አመታት ጥላ የነበረዉን ክልከላ ባለፈዉ አመት ማንሳቷ ይታወሳል። ነገር ግን ዉሳኔው በታዋቂ የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጭምር በደረሰበት ተቃዉሞ በፍርድ ቤት ታግዶ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ጉዳዩን በተመለከተ በኦንላይንም እና ህብረተሰብ ዉስጥ የሚሰራጩ ሀሰተኛ እና ትክክለኛነታቸዉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች መበራከታቸዉን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል። ከነዚህ መካከልም ‘ሰው ሠራሽ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገባቸው የእህል ዘሮች በሰዎች ላይ የጾታ ለዉጥ ያስከትላሉ’ የሚል ትክክለኛነቱ በሳይንስ ያልተረጋገጠ መረጃ እንደሚገኝበት ተዘግቧል።
- በሴራሊዮን የሀሰተኛ መረጃዎች እና ጥላቻ ንግግርን ለመግታት አይ ቬሪፋይ (iVerify) የተሰኘ ድረ-ገጽ ስራ ጀመረ። በሴራሊዮን ጋዜጠኞች ማህበር እና ኢንዲፔንደንት ራዲዮ ኔትወርክ (IRN) ይፋ የተደረገው ይህ ድረ-ገጽ ጤናማ የሆነ የመረጃ ምህዳርን ለመፍጠር የሚደረገዉን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተነግሯል። ከUNDP ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየዉ ሀገሪቱ በዚህ ወር በምታካሂደዉ አጠቃላይ ምርጫ የሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን ስርጭት በመዋጋት ረገድ አይ ቬሪፋይ ተስፋ ተጥሎበታል። በተጨማሪም ኢንተርኔት ተጠቃሚ ያልሆኑ የሀገሪቱን ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ኢንዲፔንደንት ራዲዮ ኔትወርክ (IRN) የተሰኘው የሀገሪቱ ሬድዮ ጣቢያ ምርጫን የተመለከቱ የተጣሩ መረጃዎችን እያቀረበ እንደሚገኝ የUNDP መረጃ ያመለክታል።
- የአዉሮፓ ህብረት የቴክኖሎጂ ተቋማት በሰው ሰራሽ አስተዉሎት ተፈብርከው በገጻቸዉ የሚሰራጩ ይዘቶች ላይ ገላጭ ምልክት እንዲያስቀምጡ ጠየቀ። ህብረቱ እንደ ጉግል፤ ፌስቡክ፤ ዩትዩብ እና ቲክቶክ ያሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት በሰው ሰራሽ አስተዉሎት ተፈብርከው በጽሁፍ፤ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስል መልኩ የሚጋሩ ይዘቶች ላይ በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የተሰሩ መሆናቸዉን የሚያሳይ መለያ እንዲያኖሩ ጠይቋል ሲል ዶቸ ቨለ በዚህ ሳምንት ዘግቧል። ይህ እርምጃ ህብረቱ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የሚያደርገዉ ጥረት አንድ አካል መሆኑም ተነግሯል።
✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:
– በሰኞ መልዕክታችን ወቅታዊ መረጃ ለሚዲያ ተቋማት መስጠት ሀሰተኛ መረጃ ለመዋጋት ያለውን አስተዋጵዖ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዳሰናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2026
– እንዲሁም ግልጽነት በጎደላቸው የግብይት ማስታወቂያዎች ከመታለላችን በፊት ማድረግ ስላሉብን ጥንቃቄዎች ጽሁፍ አቅርበናል፡
https://t.me/ethiopiacheck/2027
– በተጨማሪም በግጭት ወቅት አዉድ በሳተ መልኩ የሚሰራጩ አሳሳች ምስሎች ሊያደርሱት ስለሚችሉ ጉዳት እና ማድረግ ስለምንችላቸዉ ጥንቃቄዎችም መረጃ አቅርበናል፡
https://t.me/ethiopiacheck/2028
– እንዲሁም በፀሀይ አማካኝነት የሚፈጠሩ ጥላዎችን በማስላት ምስሎችን እንዴት ማጣራት እነደምንችል የሚያሳይ የቪዲዮ መረጃም አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2029
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
