በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ የተፈጠረ አሰጣገባ በቲክቶክ ያሰራጨ ግለሰብ ተከሰሰ

መስከረም 03፣ 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
1. የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች በአንዱ ላይ የአየር መንገዱን መልካም ስም ለማጉደፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒውተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ እንደቀረበበት ፋና ዘግቧል። ክሱ የቀረበበት ተከሳሽ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ነው። ተከሳሹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነ አውሮፕላን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረን እሰጣገባ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ባሉት የቲክቶክ አካውንት በቀጥታ ሲያሰራጭ እንደነበር ይታወሳል።
2. በደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል ከሚገኙ አገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት በተቀናጀ መልኩ ለመቀነስ ያለመ የድጊት መርሐ ግብር ማጽደቃቸውን አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌደሬሽን በድረገጹ አስነብቧል። የድርጊት መርሐግብሩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን በማጎልበት፣ ጋዜጠኞችን በማሰልጠን እንዲሁም የመረጃ ማጣራት ስራን በክፍለ አህጉሩ በማቀናጀት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። ከቦትስዋና፣ አንጎላ፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባብዌ፣ ናምቢያና ዛምቢያ የተውጣጡት ጋዜጠኞች የድጊት መርሐ ግብሩን ያዘጋጁት ከዩኔስኮና ከኣአፍሪካ ጋዜጠኞች ፌደሬሽን ጋር በመሆን ነው።
3. አውስትራሊያ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃን በመቆጣጠር ረገድ ግዴታቸውን የማይወጡ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን የሚቀጣ ህግ ወደትግበራ ልታስገባ መሆኑን አለማቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የሀገሪቱ ፓርላማ በመጭው ማክሰኞ ያጸድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው ህግ ግዴታቸውን በማይወጡ ኩባንያዎች ከአለም አቀፍ ገቢያቸው ላይ እስከ በመቶ ቅጣት ይጥልባቸዋል ተብሏል። ህጉ በተለይም ከምርጫና ከጤና ጋር የተገናኙ ሀሠተኛ መረጃዎችን በማይቆጣጠሩት ላይ ጫን እንደሚል ተጠቅሷል። በአንጻሩ የህጉ መጽደቅ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሊጋፋ ይችላል የሚሉ አካላት ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-በአዲሱ አመት የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቀነስ የበኩላችንን አዎንታዊ ሚና እንዴት መወጣት እንደምንችል የሚያስረዳ ጽሁፍ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2440
-በአዲስ አበባ ከተማ የተደረገ የተኩስ ልውውጥ ነው ተብሎ የተጋራ ቪድዮ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2441
-ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ ተደርጎ የተሰራ የስክሪን ቅጅን ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2443
-የጥላቻ መልዕክቶችን የተመለከተ ማብራሪም በትግርኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2445
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
