ይህ ምስል ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አያሳይም

ነሐሴ 01፣ 2015 ዓ.ም
ይህ ከታች የሚታየውን ምስል ከሰሞኑ በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት የተማረኩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሆኑ በመግለጽ የተለያዩ የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች ሲጋሩት ተመልክተናል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተነሳ እንዳልሆነ አረጋግጧል።
ምስሉ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ወቅት ከወራት በፊት በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲጋራ የነበረ እንደሆነም ተመልክተናል፣ ይህ አንዱ ማሳያ ነው: https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02F7HpZbVnkcXZ6225ecDL1ZtKLPDPABQ8aGqyHSeeVqeEPoMMfSZtPYU9hFch7Yeql&id=100429482438237&mibextid=qC1gEa
ከአውድ ውጪ በተሳሳሳተ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
