አርቲስት ቴዲ አፍሮ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት እንዳስተላለፈ ተደርጎ የተሰራጨ ሀሰተኛ ደብዳቤ

A fake letter circulating under the name of artist Teddy Afro addressing current affairs in Ethiopia

ነሐሴ 10፣ 2015 ዓ.ም

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት እንዳስተላለፈ ተደርጎ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨ ሀሰተኛ ደብዳቤ እንዳለ ተመልክተናል።

ደብዳቤው የአርቲስቱን ፊርማ በቅንብር በማስገባት የተዘጋጀ እንደሆነ ማየት የቻልን ሲሆን ይህ ደብዳቤም የቴዲ አፍሮ የተረጋገጠ የፌስቡክ አካውንት ላይ ተለጥፎ አይገኝም።

በዚህ ዙርያ ያነጋገርናቸው የአርቲስቱ ባልደረቦች ጨምረው እንዳረጋገጡት ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ደብዳቤ “ሀሰተኛ” ነው።

በቅንብር ተሰርተው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሚቀርቡ ሀሰተኛ የፅሁፍ፣ የምስል፣ የድምፅ እንዲሁም የቪድዮ መረጃዎች ራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::