የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ በፍጥነት እናስቀጥራለን በሚል በሚፈፀም ማጭበርበር ዙርያ ዛሬ ያወጣው ማሳሰቢያ

የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ በፍጥነት እናስቀጥራለን በሚል በሚፈፀም ማጭበርበር ዙርያ ዛሬ ያወጣው ማሳሰቢያ

ሐምሌ 2፣ 2017

ቪዛ እናስመታለን፣ በፍጥነት እናስጨርሳለን፣ የውጭ የትምህርት ዕድል እናስገኛለን፣ ስራ እናስቀጥራለን ወዘተ የሚሉ የማጭበርበርያ ስልቶች እየተስፋፉ እንደሆነ በቅርብ ጊዜያት የሰራናቸው የማጣራት ስራዎች ይጠቁማሉ።

አሁን ደግሞ ሶሻል ሚድያ ላይ የአሜሪካ ቪዛ በፍጥነት እናስቀጥራለን በሚል የማጭበርበር ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ያወጣው መረጃ ያሳያል።

እነዚህ የኤምባሲውን ማህተም እና ሎጎ አስመስሎ በመጠቀም የሚፈፀሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሀሰተኞች መሆናቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።

“እነዚህ አገልግሎት እንሰጣለን የሚሉ አካላት ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት የላቸውም። ማንኛውም ግለሰብ፣ አገልግሎት ወይም ማስታወቂያ ፈጣን የቪዛ ቀጠሮ ማሰጠት አይችልም፣ የቪዛ ማግኘት እድልንም ሊያሰፋ አይችልም” በማለት ኤምባሲው ማሳሰቢያውን አጋርቷል።

አንድ አካል የኤምባሲውን ማህተም እና ሎጎ ተጠቀመ ማለት ትክክለኛ ነው ማለት እንዳልሆነ የጠቆመው ኤምባሲው ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ኦፊሴላዊ የማህበራዊ አካውንቶቹን እና ትክክለኛውን ድረ-ገፁን በመጎብኘት ማግኘት ይቻላል ብሏል። ድረ ገፁ: https://et.usembassy.gov/visas/

ኢትዮጵያ ቼክ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::