እርዳታ አድርጉልን በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሚንቀሳቀሱ አንዳንድ አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ

scammers operating on social media claiming help.

መስከረም 02፣ 2017 ዓ.ም

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ‘ሙሀመድ የረሱል ወዳጅ’ በሚል ስም በተከፈተ የፌስቡክ አካውንት አማካኝነት እርዳታ በመጠየቅ ስም የሚከናወን የማጭበርበር ድርጊት ነው።

የዚህ አካውንት ባለቤት ‘ለልጄ ደብተር እና ቦርሳ ግዙልኝ’ የሚሉ መልዕክቶችን የተለያዩ የፌስቡክ ግሩፖች እና ገፆች ኮመንት ላይ በማስቀመጥ በርካታ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል/ቆይታለች። ኢትዮጵያ ቼክ እንዳረጋገጠው በዚህ መልኩ ከአንድ ግለሰብ ብቻ 30 ሺህ ብር ማግኘት ችሎ/ችላ ነበር።

ነገር ግን የዚህ አካውንት ባለቤት ለእርዳታ ጥየቃ የሚጠቀሙበት ፎቶ ከማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሰዎች አካውንት በመውሰድ ሲሆን በህይወት የሌሉ ሰዎችን ጭምር እንደተጠቀሙ ያደረግነው ማጣራት ያሳያል።

በዚሁ ተመሳሳይ አካውንት ከወራት በፊት ደግሞ ለኩላሊት ህክምና የሚሆን ብር ሲሰበሰብበት እንደነበር ደርሰንበታል። ይሁንና የማጭበርበር ድርጊቱ ሲታወቅ አካውንቱን ዘግተውታል።

ይህ የሚያሳየን የህዝብን የመደጋገፍ እና የሀዘኔታ ስሜት በመረዳት በርካቶች ማህበራዊ ሚድያን ለማጭበርበር ድርጊት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው።

የድጋፍ ጥያቄ ሲመጣ በግላችን የተቻለንን ያህል ማጣራት ሳናደርግ፣ በአካል ሁኔታውን ሳናይ ወይም ከምናምናቸው ምንጮች ካልመጣ በቀር ለእንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች እንዳንጋለጥ ጥንቃቄ እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::