የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
መስከረም 17፣ 2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ
1. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኛ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ከስደተኞችና ከጥገኝነት ጠያቂዎች አንጻር በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰነዘሩ የጥላቻ መልዕክቶች በእጅጉ እንዳሳሰቡት አስታወቀ። ኮሚሽኑ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰነዘሩ የጥላቻ መልዕክቶች መሬት ወርደው ጉዳት እያስከተሉ መሆናቸውን ጠቅሶ እንዲህ ያሉ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ አካላት ከጥላቻ ይልቅ ደግነትን እንዲሰብኩ ተማጽኗል።
2. ቴሌግራም ከፖሊሲዎቹ ተጻራሪ የሆኑ ይዘቶችን ባለፉት ሳምንታት በስፋት ማስወገድ መጀመሩን አስታውቋል። የቴሌግራም መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቬል ዱሮቭ በሳምንቱ መጀመሪያ ባስነበበው መልዕክት አስተናባሪዎችን ከ ኤአይ (AI) ጋር በማቀናጀት ችግር ፈጣሪ ይዘቶችን የማጽዳት ስራ መሰራቱን ገልጿል። የቴሌግራም ተጠቃሚዎችም አሉታዊ ይዘቶችን ሲመለከቱ @SearchReport አማካኝነት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። ዱሮቭ በፈረንሳይ ፖሊስ ታስሮ ከተለቀቀ ወዲህ የቴሌግራምን ቁጥ ጥር ጠበቅ የሚያደርጉ እርምጃዎችን ሲወስድ ታይቷል።
3. ጤና ነክ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት ለመቀነስ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር መስራት መጀመሩን ቲክቶክ በትናትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በዚህም ፊድስ (Fides) በመባል የሚታወቀው የህክምና ባለሙያዎች ትስስር ጤና ነክ ማብራሪያዎችንና የምርምር ውጤቶችን ለቲክቶክ ተጠቃሚዎች የሚያደርስበት ሁኔታ ይመቻቻል ተብሏል። ከአራት አመት በፊት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመቀናጀት የተመሰረተው ፊድስ የህክምና ባለሙያዎች ትስስር በመላው አለም ከ800 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች በምርምር የተደገፉ የጤና መርጃዎችን በማካፈል ይታወቃል። ጤና ነክ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች ቲክቶክን ጨምሮ በሌሎች ፕላትፎርሞች ከሰፊው እንደሚሰራጩ ጥናቶች ያሳያሉ።
በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-በሰኞ መልዕክታችን የሀሰተኛ መረጃ ምንጮችን የተመለከተ ጽሁፍ በትግረኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2456
-በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች የተቃጠሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ፎቶዎችን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2457
-አቶ ስብሃት ነጋን (አቦይ ስብሃትን) በተመለከተ የተሰራጨን መረጃም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2459
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::