እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ወታደሮችን ያሳያል ተብለው የተለቀቁት ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው

የካቲት 26፣ 2018

እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ወታደሮችን ያሳያል ተብለው የተለቀቁት ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው
/ኢትዮጵያ ቼክ/- በቅርብ ግዜያት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ መልእክቶች በፅሁፍ፣ በቪዲዮ፣ በምስል እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በታገዙ ምርቶች በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
ከነዚህም መሀል ‘ፍፁም ተስፋዬ’ በሚል ስም የተከፈተ ከ33,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ 318 የኤርትራ ወታደሮች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን በመጥቀስ መረጃ አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጀ 58 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 211 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።
በተመሳሳይ መልኩ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የተባለ ከ26,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅም ምስሉን እና መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ ደግሞ 67 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 192 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።
በተጨማሪም ‘Betty Gullele’ በሚል ስም የተከፈተ ከ55,000 በላይ ተከታዮች ያለው የፌስቡክ ገፅ መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ አራት ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 18 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ መከላከያ እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ሰራዊት አባላት እንደማያሳይ አረጋግጧል።
የጉግልን ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Lens) በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የኤርትራ ጦር ከሶስት አመት በፊት ከትግራይ ክልል አካባቢዎች ሲወጣ የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠናል (ማስረጃ https://x.com/i/status/1616523677885169666
ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ በሆነ መልክ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።
ኢትዮጵያ ቼክ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::