በኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረስላሴ ታምራት ስም ከተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች እንጠንቀቅ

ሚያዝያ 2፣ 2018

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ሚስጥረስላሴ ታምራትን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች የተለያዩ መረጃዎችን እያጋሩ መሆናቸዉን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገዉ ማጣራት በርከት ያሉ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች በዋና ጸሐፊዋ ስም መከፈታቸዉን አረጋግጧል።

በሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶቹ ከተጋሩ መረጃዎች መካከል 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተገናኘ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ንግግሮች ይገኙበታል።

ዋና ጸሐፊዋ ከቀናት በፊት በትክክለኛ የፌስቡክ አካውንታቸው ባጋሩት ጽሁፍ “በስሜ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተከፈቱና እኔን የማይገልጹ ጽሁፎች እንዲሁም ፎቶዎች ተቀናብረው እየተለቀቁባቸው መሆኑን ተመልክቻለሁ” ብለዋል።

በተጨማሪም ትክክለኛ አካውንታቸዉ ከ55 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል፡ https://www.facebook.com/share/17f9UcAsUC/?mibextid=wwXIfr

የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እና ምስል (አርማ) በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ተገቢዉን ጥንቃቄ እናድርግ።

በተጨማሪም ሀሰተኛ እና ተመሳስለዉ የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገጾችን እና ቻነሎችን ለመለየት የሚረዱን ጠቋሚ ምልክቶችን ለማየት ይህን በኢትዮጵያ ቼክ የተዘጋጀን አጭር ቪድዮ ይመልከቱ፡ https://t.me/ethiopiacheck/1344

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::