በአዲስ አበባ የጦር አውሮፕላኖች ዝቅ ብለው ሲበሩ የታየዉ ለአድዋ በዓል ለሚቀርብ ትርዒት የተደረገ ልምምድ መሆኑን መከላከያ አስታወቀ

በአዲስ አበባ የጦር አውሮፕላኖች ዝቅ ብለው ሲበሩ የታየዉ ለአድዋ በዓል ለሚቀርብ ትርዒት የተደረገ ልምምድ መሆኑን መከላከያ አስታወቀ

የካቲት 21፣2015

ዛሬ እኩለ ቀን ላይ በአዲስ አበባ የጦር አውሮፕላኖች ዝቅ ብለው በፍጥነት ሲበሩ ተስተውሏል፣ ይህን ተከትሎም በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ መላ ምቶች ሲሰጡ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነን ጠይቋል።

ኮሎኔሉ የጦር አውሮፕላኖች ልምምድ እያደረጉ መሆናቸው የገለጹ ሲሆን ልምምዱም በመጨው ሀሙስ በሚከበረው የአድዋ በዓል ለሚቀርብ ትርዒት መሆኑን አስታውቀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ አንድ የአቪዬሽን ባለሙያ የፍላይት ራዳር መረጃን በመጥቀስ በሰጠን አስተያየት “የጦር ጀቶቹ ሲበሩ የነበረው ለመሬት ዝቅ ብለው እና በእጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ነበር” ብሏል።

ባለሙያው አክሎም “ለዚህ ልምምድ የአዲስ አበባ የአየር ክልል ለበርካታ ደቂቃዎች ዝግ ተደርጎ ነበር” ብሎ አስረድቷል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::