ይህ የሞቱ ወታደሮች በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚያሳይ ቪዲዮ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ አይደለም

መስከረም 29፣ 2017 ዓ.ም
ከ600 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Astuka ከሐረር’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ/ትዊተር አካውንት የሞቱ ሰዎችን በቃሬዛ ተሸክመው ወደ ሄሊኮፕተር የሚወስዱ ወታደሮችን የሚያሳይ ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል። አካውንቱ ቪዲዮው ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ መሆኑን ለማስረዳት ሲሞክር ታዝበናል።
ቪድዮው ሙሉ እይታ እንዳይኖረው ከፊል ይዘቱ በጽሁፍ የተሸፈነ ቢሆንም ከ11,000 በላይ ጎብኝዎችን መሳቡንም አይተናል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጋራው ቪድዮ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ አለመሆኑን አረጋግጧል። ቪዲዮው የተቀረጸው በደቡባዊ ሊባኖስ ሲሆን በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚታዩትም በሂዝቦላ የተገደሉ ስምንት የእስራኤል ወታደሮች ናቸው።
ቪዲዮውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከቀናት በፊት ለዘገባ የተጠቀመበት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል መመልከት ይቻላል: https://www.youtube.com/watch?v=ZRWocGEqwWY
ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
