ምስሎችን ለማጣራት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው መተግበሪያዎች!

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ መረጃዎች ይሰራጫሉ፣ በተለይም ምርጫ እየቀረበ ሲመጣ የሚሰራጩየሀሰት መረጃዎች ይበዛሉ። እነዚህ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማጣራት የሚያግዙ ከድረገጾች እስከ ሞባይልመተግበሪያዎች ድረስ የተለያዩ መሳሪያዎች አሉ።

ከእነሱም መካከል የተወሰኑትን እናስተዋውቃችሁ:

1. ጉግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች(google reverse image search): ይህ መተግበሪያ ምስሎችን በኢንተርኔት አማካኝነትለማጣራት የሚጠቅመን መሳሪያ ነው። አጠቃቀሙ ደግሞ ጉግል ውስጥ በመግባት ድረገጹ ላይ የሚታየውንምስሎችየሚለውን በመምረጥ ለማረጋገጥ የፈለግነውን ምስል ከኮምፒተር ወይም ከስልካችን ላይ መርጠንበማስገባት የካሜራ ምልክቱን መጫን ነው።

2.  ቲንአይ(TinEye): ይህ መተግበሪያ ምስሎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማጣራት የሚጠቅመን ድረገጽ ነው።የምንፈልገው ምስል ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ ከነበረ መቼ እና የት ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳውቀናል። በዚህመተግበርያ በፎቶሾፕ የተነካኩ ምስሎችንም ፈልጎ ማግኘት ይቻላል።

3.  ፎቶ ፎሬንዚክስ(Photo Forensics): ይህ መተግበርያ የሚጠቅመን የአንድን ፎቶ በፎቶሾፕም ሆነ በሌላሶፍትዌር አለመነካካቱን እና ከዋናው ፎቶ አለመቀየሩን ነው። አጠቃቀሙ: በመጀመሪያ ወደwww.fotoforensics.com ከገባን በሁዋላ በመጀመሪያው ገጽ ማረጋገጥ የምንፈለገውን ፎቶ የምናስገባበት ገጽእናገኛለን። የምንፈልገውን ፎቶ ከኮምፒተራችን ወይም ከስልካችን መርጠን ካስገባን በሗላ ፈልጎ ሲጨርስፎቶው ተነካክቶ ከሆነ ምኑ ጋር እንደተነካካ ወይም እንደተቀየረ የሚያሳየን ፎቶ ይመጣል። ያስገባነው ፎቶ ላይተመሳሳይ ቀለም ብቻ የምናይ ከሆነ ፎቶ እውነተኛ ፎቶ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን። አንድ ቦታ ላይ በብዛትለየት ያለ ቀለም ወይም ነጣ ያለ ቀለም አንድ ቦታ ላይ ተከማችቶ ካገኘን ፎቶ መነካካቱን መረጋገጥ እንችላለን።

ከእነዚህ በተጨማሪ እንደ ሰርች ባይ ኢሜጅ (Search by Image) ካምፋይንድ(CamFind) ጉግል ሌንስ (Google Lens) እና የመሳሰሉት የተባሉ መተግበሪያዎችም ይገኛሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::