የጀርመን ድምፅ የአማርኛ አገልግሎት ዛሬ መረጃ ያጣቀሰበት የፌስቡክ ገፅ ጉዳይ! 

ዛሬ የጀርመን ድምጽ የአማርኛ አገልግሎት ከዓሲባ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ዓዴፓ) የፌስቡክ ገጽ አገኘሁት ባለው መረጃ ተመስርቶ ዘገባ ሰርቶ ነበር። ከጀርመን ድምጽ በተጨማሪ አንዳድ የዩቱብ ቻናሎችና የፌስቡክ ገጾች በዓሲምባ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ስም የተከፈተና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትን የፌስቡክ ገጽ ዋቢ በማድረግ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መረጃ ሲያሰራጩ ተመልክተናል። 

የዓዴፓ ሊቀመንበር አቶ ዶሪ አስገዶም ከወራት በፊት ይህ የፌስቡክ ገጽ የፓርቲያቸው አለመሆኑን ገለጸው ነበር። 

የጀርመን ድምጽ የአማርኛ አገልግሎት ከደቂቃዎች በኃላ ዘገባውን ከማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ የሰረዘ ሲሆን፣ የፌስቡክ ገጹን ትክክለኛነት ለማጣራት እየጣረ መሆኑን አስታውቋል። 

ከሳምንት በፊት CNN በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ስም የተከፈተን ሀሠተኛ አካውንትን ዋቢ በማድረግ ዘገባ መስራቱ የሚታወስ ሲሆን ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ሀሠተኛነት ካጋለጠ በኃላ የዕርምት እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::