በዲጂታል ዘመን ምርጫ እና ፈተናዎቹ!

መንግስት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሰዎች ሀሳብን በነፃነት የመናገር መብትን ለመገደብ ሲሰሩ ይታያሉ። በተለይ ደግሞ በምርጫ ወቅት። ከነዚህም ውስጥ 

1. የኢንተርኔት መዘጋት

በርከት ያሉ መንግስታት ኢንተርኔትን በመዝጋት እና ቴሌኮሚኒኬሽን በማቋረጥ የፍትሃዊ የምርጫ ስርዓቱን ሲያስተጓጉሉ ይታያሉ። ኔትወርክን ማቋረጥ ሰዎች ማግኘት ያለባቸውን መረጃ ሆን ተብሎ በማቋረጥ የሰዎችን የሰብዓዊ መብትን መጋፋት ነው። ኔትወርክን ማቋረጥ የዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት

አንቀጽ 19(3) ጋር በግልፅ ይቃረናል። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ እንዳስቀመጠው ከሆነ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የኔትወርክ  ማቋረጥ ተገቢ ሊሆን አይችልም ይላል። ለህብረተሰቡ ደህንነት በሚልም ሆነ ለብሄራዊ ደህንነት ሲባል የኔትወርክ መቋረጥን እንደተገቢ እርምጃ መውሰድ አይቻልም። የኔትወርክ መቋረጥ የተለያየ መልክ ሊይዝ ይችላል እነሱም  ኢንተርኔትን መዘጋት፣ የስልክ ኔትወርክን ማቋረጥ፣ የአጭር የስልክ መልዕክትን መዘጋት፣ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ መዘጋት ሊሆኑ ይችላል። በተለይ በምርጫ ወቅት የኔትወርክ መቋረጥ ከፍተኛ ጉዳትን ይዞ ይመጣል። ስለምርጫው አጠቃላይ ስለሚወጡ መረጃዎች፣ ስለ እጩ ተወዳዳሪዎች አቋም፣ በምርጫው ቀን ደግሞ ስለምርጫ ጣቢያዎች እና የመሳሳሰሉትን መረጃዎች ሰዎች እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። ይህም ደግሞ በተዘዋዋሪ የዜጎችን በነፃ እና በግልፅ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ተሳትፎ ያግዳል።  

2. የሀሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስታት የሀሰተኛ መረጃን ስርጭት ለመቀነስ/ለመቆጣጠር ሲባል የተለያዩ ህጎችን እና መመሪያዎች ሲያፀድቁ አይተናል። የሀሰተኛ መረጃዎች መሰራጨት በመራጮች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ በዴሞክራሲ አውዱ ላይ ብዙ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ምንም ጥርጥር የለም። ሆኖም ግን መንግስታት የዚህን የሀሰተኛ መረጃ መበራከትን ተገን በማድረግ በሰዎች ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በሚያግዱ መልኩ የተለያዩ ህጎች እና መመሪያዎች ሲወጡ ይስተዋላል። በአብዛኛው ጊዜ እነዚህ ህጎች ስለ ሀሰተኛ መረጃ ምንነት በደንብ ባልገለፀ መልኩ ይወጣሉ።ይህም ሲሆን ለአስፈፃሚ አካላት ህጉን እንደሚፈልጉት እንዲተረጉሙት ክፍተትን ይፈጥርላቸዋል። 

3. አገልግሎትን መከልከል

በምርጫ ወቅት መንግስታት የማይፈልጉት/እነሱን የሚጎዳ ሀሳቦች እንዳይንሸራሸሩ ሲገድቡ ይስተዋላሉ። በዚህ በዲጂታል ዘመን ላይ ደግሞ የዚህን ሀሳብን የመገደብን አካሄድ ዘርፈ ብዙ አድርገውታል። የተሰራጨ አገልግሎትን መከልከል (Distributed Denial of Service) ብዛት ያላቸው እና በኔትወርክ የተያያዙ ሌላን ሲስተም, በይነመረብ, ማህበራዊ ገፅን በተመሳሳይ ሰዓት በመጠቀም እና በማጨናነቅ ያንን ድህረገፅ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ የሚፈልገው ሰው ማግኘት እንዳይችል ሜድረግ ነው:: በብዛት የሚታየው የተሰራጨ የአገልግሎት ክልከላ (Distributed Denial of Service) የተመራጡ ድረ ገጾች፣ ማሕበራዊ ሚዲያዎች ወይም ኮምፒተርን በብዛት በማጥለቅለቅ ወይም በማበላሸት በአዘውታሪዎቹ እንዳይገኝ ማድረግ ማለት ነው፡፡

4. በመራጮች መዝገብ እና በመራጮች መረጃ ላይ ጣልቃ መግባት 

በምርጫሂደት ላይ ሌላው ችግር የሚፈጥረው ነገር በመራጮች መዝገብ እና በመራጮች መረጃ ላይ ጣልቃ መግባት ነው።በተለያዩ መንገዶች የመራጮች መረጃ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል። 

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያሉ የሰዎች መረጃዎችም አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ።

በምርጫ ወቅት በዚህ የቴክኖሎዎጂ ዘመን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች አይነታቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ማየት እንደቻልነው ከሆነ የኔትወርክ መቋረጥ የሰዎችን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ሲጋፋ የሀሰተኛ መረጃ መዛባት ደግሞ በምርጫ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል በዚህም ምክንያት መንግስታት ይህን እንደ ምክንያትነት በመጠቀም የሰዎችን መረጃ የማግኘት መብትን ሲጋፉ እናያለን:: 

የመንግስት አካላት ኔትወርክን ከመዝጋት ይልቅ የተለያዩ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ስለምርጫ እና ስለሀሰተኛ መረጃ መዛባት ዙሪያ ጥናቶችን ማካሄድ፤የነዚህ የመረጃ ማሰራጫ ድርጅቶች ደግሞ ሀላፊነትን ወስደው እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።

ምንጭ- OHCHR special procedures, mandate of the special rapporteur on the promotion and protection of the right to freedom of opinion and expression.

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::