የዓለም የፀረ-ጥላቻ ቀን ሆኖ ለመጀመርያ ግዜ ታስቦ ውሏል!

ሰኔ 11 (June 18) የፀረ-ጥላቻ ቀን እንዲሆን የተወሰነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በሀምሌ ወር 2013 ዓ.ም ጥላቻ በማህበረሰቦች ዘንድ እያደረሰ ያለው ምስቅልቅሎሽ ተወያይቶ፣ መገታት እንዳለበትም ስምምነት ላይ ደርሶ የውሳኔ ሀሳብ (resolution) ካሳለፈ በኋላ ነበር።

ቀኑ በመላው ዓለም ዛሬ በተለያዩ ክንውኖች በመከበር ላይ ሲሆን በተለይም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥላቻ የሚያደርሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት በማስታወስ መቻቻልና አጋርነትን የሚያበረታቱ መልዕክቶች ሲተላለፉ አስተውለናል። #NoToHate የሚል ሃሽታግ የመልዕክቶቹ ሰብሳቢ ሆኖ ውሏል።

እኛም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ወይም በነባራዊ ዓለም የሚተላለፉ ጥላቻ አዘል መልዕክቶች መሬት ወርደው ለሰዎች ሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅሎሽ እንደሚዳርጉ ተገንዝበን መቻቻልንና አጋርነትን በማበረታታት ከጥላቻ በተቃራኒ ለመቆም ቃል የምንገባበት ዕለት እንዲሆን መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::