ኤርትራን በተመለከተ የተሰራጨው ይህ መረጃ የተሳሳተ ነው!
መጋቢት 24፣ 2017
‘ESAT In Ethiopia’ በሚል ስያሜ ትክክለኛውን የኢሳት የፌስቡክ ገፅ በማስመሰል የተከፈተ ይህ ገፅ ‘ሰበር ዜና’ በማለት አንድ መረጃ በትናንትናው እለት አጋርቷል።
“የኤርትራ መንግስት በኮንፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሀድ በሚያስችል ሁኔታ ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ሲል ለአሜሪካው ኘሬዚዳንት ትላንት መግለፃቸው ተሰማ!” በሚል የቀረበው ይህ መረጃ በበርካታ ሰዎች አስተያየት ተሰጥቶበታል፣ አንዳንዶችም አጋርተውታል።
ይሁንና ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት የኤርትራ መንግስት እንዲህ አይነት መረጃ ለአሜሪካ መንግስት እንዳላቀረበ ማረጋገጥ ችለናል።
ዳሰሳ ያደረግንባቸው የሚድያ ሪፖርቶች፣ የመንግስታቱ መግለጫዎች እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ምንጮች መረጃው ሀሰተኛ መሆኑን ይጠቁማሉ። መረጃው የተሰራጨበት የፌስቡክ ገፅም ተመሳስሎ የተከፈተ እንጂ የኢሳት እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ችለናል።
ተመሳስለው የሚከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች፣ ገፆች እና ቻናሎች ለሀሰተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ አይለየን።
ኢትዮጵያ ቼክ!
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::