በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ አካውንት
ሐምሌ 23፣ 2016 ዓ.ም
ከቅርብ ግዚያት ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪ ግለሰቦች የገንዘብ ሚኒስቴርን አርማና የሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ፎቶን በመጠቀም በተለያዩ ድረ-ገጾችና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ገንዘብ ሚኒስቴር ለስራ ፈጣሪዎችና ለግል ድርጅቶች የሚሰጥ የድጋፍ ገንዘብ ያዘጋጀ በማስመሰል ግለሰቦች እንዲያመለክቱና መመዝገቢያ ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
እነዚህ አጭበርባሪ አካላት በተለይም ገንዘብ ሚኒስቴር ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የሚያደርገውን የልማት ድጋፍና የብድር ስምምትን እየተከተሉና የቅርብ ጊዜ የሚኒስትሩንና የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሀላፊዎችን ፎቶ በማስደገፍ ግለሰቦች ለገንዘብ ድጋፉ እንዲመዘገቡና ፎርም እንዲሞሉ እየወተወቱ ስለሆነ ህብረተሰቡ ከነዚህ አጭበርባሪዎች ራሱን አንዲጠብቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።
“በተጨማሪም ህብረተሰቡ ገንዘብ ሚኒስቴር በህግ ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት ውጪ ለግለሰቦች፣ ለስራ ፈጣሪዎችና ለግል ድርጅቶች ገንዘብ የሚያከፋፍልበት አሰራር እንደሌለው አውቆ እንዳይታለል እያሳሰብን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር በአጭበርባሪዎች ላይ ክትትል እያደግን መሆናችንን እናሳውቃለን” ብሏል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::