በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው!

በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው

መጋቢት 6፣ 2017

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የአፍሪካ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ አበበ አእምሮ ሥላሴ ስም እና ፎቶ (Profile Picture) የተከፈተ አንድ የፌስቡክ ገፅ ከሰሞኑ በርካታ መልዕክቶችን እያስተላለፈ ይገኛል።

ይህ ከ2,500 በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ አቶ አበበ የሚመሩት ተቋም የተለያዩ የኢንቨስትመንት እድሎችን እንደሚደግፍ በመግለፅ ለተለያዩ ግለሰቦች በመደወል እና የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ቼክ አቶ አበበን በዚህ ዙርያ ያነጋገረ ሲሆን እርሳቸውም ከኤክስ (ትዊተር) ውጪ ፌስቡክ እንደማይጠቀሙ እና የፌስቡክ ገፁም የእርሳቸው እንዳልሆነ አስረድተዋል። ትክክለኛው የኤክስ አካውንታቸው ይህ ነው: https://x.com/aselassie?t=2d32OlM5ich2aRP5JZDRcg&s=09

ተመሳስለው የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች፣ አካውንቶች እና ቻናሎች ለመጭበርበር፣ ለጥላቻ ንግግሮች እና ለሀሰተኛ መረጃ ስለሚያጋልጡን የምንከተላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን እስከምናረጋግጥ ድረስ ጥንቃቄ አይለየን።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::