የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ስንት ደርሷል?

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለህዝብ እንደራሴዎች ጥያቄዎች መልስ በሰጡበት ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት 33 በመቶ መድረሱ ተጠቅሷል።

በዚሁ ወቅት በተለያዩ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምክንያቶች እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነትን ከሌሎች ዓለም አገራት ካለው የዋጋ ግሽበት ጋር በንፅፅር የቀረበ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለው የዋጋ ግሽበት 33 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃዎች ላይ ዳሰሳ አድርጓል።

የስታቲስቲክስ አገልግሎቱ ባወጣው የመጨረሻው (latest) የግንቦት ወር ሀገራዊ ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደጠቀሰው በግንቦት ወር የምግብ የኢንዴክሱ ክፍሎች መጠነኛ ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን ምግብ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች ላይ የመረጋጋት ሁኔታ ታይቷል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ በግንቦት ወር 2014 ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 37.2 ከመቶ መሆኑን ተቋሙ ይፋ አድርጓል። ይህም አሁን ያለው የዋጋ ግሽበት 33 በመቶ ነው ተብሎ ለህዝብ እንደራሴዎች ዛሬ ከቀረበው ጋር የሚጣረስ መሆኑን ማየት ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::