‘ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት አበድሮ ያልመለሰለት ገንዘብ 92.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ’ በሚል እየተሰራጨ ያለው ዜና ከዘጠኝ አመት በፊት የተሰራ ዘገባ ነው

'ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት አበድሮ ያልመለሰለት ገንዘብ 92.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ' በሚል እየተሰራጨ ያለው ዜና ከዘጠኝ አመት በፊት የተሰራ ዘገባ ነው

የካቲት 20፣ 2017

ሪፖርተር ጋዜጣ የዛሬ ዘጠኝ አመት ገደማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፌዴራል መንግሥት በጀት መሸፈኛ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ ያልተመለሰለት 92.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ዘግቦ ነበር።

ጋዜጣው በዘገባው ላይ ባንኩ በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግሥት አበድሮ ያልተመለሰለት ገንዘብ 83.2 ቢሊዮን ብር ወይም 90.3 በመቶ ሲሆን፣ ቀሪው 9.7 በመቶ ደግሞ በቦንድ ተበድሮ ያልተመለሰለት መሆኑን ጠቅሶ ነበር።

ይሁንና ይህ የሪፖርተር ዘገባ የታተመበት ጋዜጣ የስክሪን ቅጂ (ስክሪንሾት) ከሰሞኑ በስፋት እየተጋራ ሲሆን መረጃው አዲስ እንደሆነ ተደርጎ እየቀረበ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ይሁንና መረጃው አዲስ ሳይሆን እ.አ.አ በፌብሪዋሪ 21/2016 የወጣ ዜና መሆኑን ማየት ችለናል።

ላለፉት 16 ዓመታት ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ሲበደር የነበረው የፌደራል መንግሥት ከአገር ውስጥ ገቢ ከ15 በመቶ የበለጠ ገንዘብ በብድር ማግኘት እንዳይችል የሚገድብ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት በፊት መቅረቡ ይታወሳል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ ካልመለሰ ከተቋሙ ሌላ ብድር መውሰድ እንደማይችልም ያስቀመጠ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::