የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋም እንደሌለ አስታወቀ

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋም እንደሌለ አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ዛሬ እንዳስታወቀው ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከፌደራል ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ ነው ብሏል፡፡
ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ስያሜ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ የሚገልጽ መልእክት በማህበራዊ ድህረ-ገጽ እየተዋወቀ እንደሚገኝ የጠቆመው ባለሥልጣኑ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት እራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው ይህ ተቋም ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ታውቆ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
ባለሥልጣኑ አክሎም በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::