ትናንት ምሽት በቦሌ አየር ማረፊያ አንዳንድ አውሮፕላኖች ማረፍ ያልቻሉት ለምን ነበር?

ትናንት ምሽት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደተዘጋ እና በረራዎችም ወደ ጅቡቲ እና ሌሎች ስፍራዎች እንደተዛወሩ የሚገልፁ መረጃዎች ወጥተዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው አንዳንድ በረራዎች ትናንት በነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ነበር፣ ወዲያው ግን በረራዎች ቀጥለው እንደነበር ታውቋል። 

ይሁንና በአየር ማረፊያው ከነበሩ የተወሰኑ ተጓዦች እና አንድ የአየር መንገዱ የስራ ሀላፊ የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው “አየር ማረፊያው ተዘጋ” በሚል የወጣው መረጃ የሀሰት ነው፣ የበረራ መስተጓጎሎች ግን ተከስተው ነበር።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::