እዚህ ፎቶ ላይ የምትታየው ግለሰብ ማን ናት? 

እዚህ ፎቶ ላይ የምትታየው ግለሰብ ማንነት እንዲሁም የፎቶው እውነተኛነት ብዙዎችን ሲያነጋግር ውሏል። አንዳንዶች የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛ እንደሆነች፣ ሌሎች ደግሞ ጋዜጠኛ እንደሆነች የገለፁ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ፎቶው በቅንብር የቀረበ እንደሆነ ለማስረዳት ሞክረዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ በርካታ ጥያቄዎች ዛሬ ቀርበውለታል። 

በምስሉ ላይ የምትታየው የፊንላንድ ተወላጅ የሆነች ጋዜጠኛ ሊንሴሎት ሊንድስትሮም (Liselott Lindstrom) ትባላለች። ጋዜጠኛዋ በናይሮቢ፣ ኬንያ መቀመጫዋን ያረገች ሲሆን Yle Uutiset እና SVT Nyheter ለተባሉ ሚድያዎች በፍሪላንስ ትሰራለች። 

ፎቶውም የተወሰደው በዛሬው እለት ለንባብ በበቃው አንድ ፅሁፏ ላይ ነው (https://yle.fi/uutiset/3-11997809)። ጋዜጠኛዋ መቼ እና እዴት ወደ ኢትዮጵያ እንደገባች እንዲሁም የጋዜጠኝነት ፍቃድ አግኝታ ይሁን አይሁን ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንቀርባለን።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::