ዋልታ ዛሬ የተሳሳተ ምስላቸውን ይዞ የወጣው ላውረንስ ፍሪማን ማን ናቸው?

ዋልታ ዛሬ “በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተሳሳተ መንገድ መተረክ የሀገሪቱን ህልውና ይፈታተናል” ብለው የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኝ የሆኑት ላውረንስ ፍሪማን መፃፋቸውን አስነብቧል። ይሁንና አያይዞ ያቀረበው ምስል ተመሳሳይ ስም ያላቸውን ቄስ ላውረንስ ፍሪማን የተባሉ ግለሰብን ነበር።

የሆነው ሆኖ እኚህ በኢትዮጵያ ዙርያ በርካታ ፅሁፎችን
http://lawrencefreemanafricaandtheworld.com/ በሚል ድረ-ገፃቸው ስለሚያስነብቡት ግለሰብ የተወሰነ መረጃ ልናቀርብ ወደድን።

ላውረንስ ፍሪማን የአፍሪካ ጉዳይ የሚያሳስባቸው እንደሆኑ የሚገልፁ ሲሆን ጡረታ ከወጡበት ከ30 ዓመት በፊት ጀምሮ ስለ አፍሪቃ ምጣኔ ሃብት፣ ኔኦ-ኮሎኒያሊዝም ወዘተ መጻፍና ማማከር መጀመራቸውን ከ3 ሳምንት በፊት ለፕራይም ቲቪ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል።

በዮንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ተጋባዥ መምህር በመሆን እንደሚያስተምሩ ከዩኒቨርስቲው ኦፊሴላዊ ድረገጽ መረዳት ችለናል፣ በቻይናው ሲጂቲኤን ድረ-ገጽም ጽሁፋቸውን ያስነብባሉ።

ላውረንስ ፍሪማን ከ4 ዓመት በፊት የከፈቱት የትዊተር አካውንት ያላቸው ሲሆን (https://twitter.com/lfreemansafrica?s=09) በርካታ ስራዎቻቸውንም ያቀርቡበታል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::