አቶ አባዱላ ገመዳ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስማቸው ስለተከፈቱት አካውንቶች እና ገፆች ምን ምላሽ አላቸው?

የቀድሞውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አባ ዱላ ገመዳን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገጾችና የትዊተር አካውንት እንዳሉ ተመልክተናል። ተከታዮቻችንም ስለአካውንቶቹ ትክክለኛነት እንድናጣራ ጠይቀውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የገጾቹንና የአካውንቶቹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አቶ አባ ዱላን አነጋግሯል።

አቶ አባ ዱላ “አኔ ምንም ማህበራዊ ሚዲያ አልጠቀምም፣ መጠቀምም አልፈልግም። የሚፅፉትንም አላይም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::