አዲስ አበባ የሚገኙት የሩስያ እና ዩክሬን ኤምባሲዎች በዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት በተሰራጨ ምስል ዙርያ ለኢትዮጵያ ቼክ ምን አሉ?

ይህ ምስል ዛሬ በስፋት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨ ሲሆን የሩሲያ ኤምባሲ የውጪ በር ላይ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሩሲያ ለመዝመት ለምዝገባ ተሰልፈው የሚያሳይ ምስል ነው ተብሏል። ምስሉ ላይ ዶክመንቶችን የያዙ በርካታ ሰዎች ይታያሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ አዲስ አበባ ከሚገኙት የሩስያ እና ዩክሬን ኤምባሲዎች መረጃ ጠይቋል።

የሩስያ ኤምባሲ መልስ: “እነዚህ ሰዎች ወደ ሩስያ ኤምባሲ የመጡት ለሩስያ እና [ለምታራምደው] ፖለቲካ ድጋፋቸውን በአካል ለማሳየት እና ለመግለፅ ነው። የተቻለውን ድጋፍ ሁሉ ለመስጠት ፍላጎታቸውን ገልፀዋል፣ ነገር ግን ኤምባሲያችን የቅጥር ድርጅት አይደለም። ለዚህ ድጋፍ ኤምባሲያችን ምስጋናውን ያቀርባል፣ ነገር ግን ምንም አይነት ቅጥር ኤምባሲያችን እያካሄደ አይደለም።”

የዩክሬን ኤምባሲ: “ይህ አሳዛኝ ድርጊት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጦርነት ህይወቱ ቢያልፍ ለዩክሬንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል።”

Photo: Social Medi

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::