አዲስ የተሾሙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ስምና ምስልን በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል!

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደተጻፈ ሆኖ የተዘጋጀና የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በየክልላቸው በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር ተመልክተናል። ደብዳቤውን የተመለከቱ ተማሪዎችም ስለትክክለኛነቱ እንድናጣራለቸው ጠይቀውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት ከጻፋቸው ደብዳቤዎች ጋር በማነጻጸር ደብዳቤውን የተመለከተ ሲሆን የፊደል ቅርጽና መጠን ልዩነት እንዳለው ተገንዝቧል። በተጨማሪም ደብዳቤ ቁጥር ያልተጻፈበት ሲሆን ሌሎች ግድፈቶችም እንዳሉበት አስተውሏል።

ኢትዮጵያ ቼክ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋገረ ሲሆን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ደብዳቤው ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በተመለከተም የተወሰነ ውሳኔ አለመኖሩን ጨምረው ገልጸዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::