የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን የተመለከቱ ግራ መጋባቶችን እንድናጣራ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶችን ተቀብለናል!

ፈተናዎቹ በኦንላይን (online) ነው ወይስ በወረቀት የሚሰጡት በሚል የተፈጠረ ግርታ እንዳለ እና ይህንንም እንድናጣራ በተጠየቅነው መሰረት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አግኝተን ነበር። 

በዚህ ጊዜ ምንም የተወሰነ ነገር እንደሌለ ለኢትዮጵያ ቼክ የተናገሩት የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ረዲ ሽፋ፣ ተማሪዎች ሁለቱንም የመፈተኛ ሁኔታዎች ታሳቢ አድርገው እንዲዘጋጁ መክረዋል። 

“ተማሪዎች ፈተናው በኦንላይን ወይም በወረቀት ሊሰጥ እንደሚችል ታሳቢ አድርገው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል:: ነገር ግን የፈተናው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለማጥራት መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል” ብለዋል። 

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ረዲ ሽፋ ፈተናዎቹ ጥቅምት አጋማሽ ላይ እንደሚሰጡ እና ፈተናዎቹ የሚሰጡበት ትክክለኛዎቹ ቀናት ጊዜው ሲቃረብ መግለጫ እንደሚሰጥ በተለይ ለኢትዮጲያ ቼክ ገልጸዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::