የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ያጣራነው የአቶ ወርቁ አይተነው ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት አሁንም ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዳለው ለማስተዋል ችለናል!

በርከት ያሉ ተከታታዮቻችን ይህ የትዊተር እና ሌሎች አካውንቶች በእርግጥ የአቶ ወርቁ ስለመሆናቸው እንድናጣራ መጠየቃቸውን ተከትሎ ባደረግነው ፍተሻ ባለሀብቱ የትዊተር አካውንት እንዴሌላቸው መግለጻቸውን ለተከታታዮቻችን አድርሰን ነበር።

“አቶ ወርቁ አንድ የፌስቡክ አካውንት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን ይህም በአሁኑ ወቅት ከ132 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ነው። ትዊተርን በተመለከተ ምንም አይነት አካውንት እንደሌላቸው ጨምረው አስታውቀዋል” በማለት በወቅቱ ማስነበባችን ይታወሳል።

የአቶ ወርቁን ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይችላሉ:- https://www.facebook.com/WAOilfabrica

ይህ አካውንት በአሁኑ ወቅት ከ157 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውጪ ያሉት ሌሎች በእርሳቸው ስም የተከፈቱ ገጾች ሀሠተኛ መሆናችውን ልናስታውስ እንወዳለን።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::