አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዲህ አይነት ፅሁፍ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል?

“ዲጂታል ወያነ” የተባለ ወደ 23,000 ገደማ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፃፉ ያለውን በምስሉ ላይ የሚታየውን ልጥፍ አጋርቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ በፌስቡክ ማረጋገጫ ያለውን (verified የሆነውን) የአቶ ተመስገንን የአሁንም ይሁን የቀድሞ ፅሁፎች የተመለከተ ሲሆን እንዲህ አይነት ፅሁፍ እንዳላጋሩ እና ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀናበረ መሆኑን አረጋግጧል።

ምስሉ ላይ የፌስቡክ ማረጋገጫ የሆነው ሰማያዊ ምልክት እና ተያይዞ የቀረበው ፅሁፍ በቅንብር እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ የሚጠቀምበት የፎቶ ፎረንሲክ መተግበርያም ይህንኑ አረጋግጧል።

በፎቶሾፕ የተቀናበሩ ምስሎች፣ ተመሳስለው የተከፈቱ አካውንቶች እንዲሁም በትክክለኛ አካውንቶች እና ገፆች የሚሰራጩ የሀሰተኛ መረጃዎች እየበዙ ይገኛሉ። የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ሲሉ እርግጠኛ ያልሆኑበትን መረጃ ለሌሎች አያጋሩ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::