ዛሬ በነበረው ሰልፍ ላይ የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ሲቃጠል የሚያሳየው ምስል ትክክለኛነቱ ምን ያህል ነው? 

ይህ የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ሲቃጠል የሚታይበት ፎቶ ዛሬ በርከት ባሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሲዘዋወር ተመልክተናል። ከፎቶው ጋር አብረው የተሰራጩ መልዕክቶች ሰንደቅ አላማ የማቃጠል ድርጊቱ በኢትዮትዮጵያውያን ስለመፈጸሙ አስነብበዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የሪቨርስ ኤሜጅ ሰርች መገልገያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ከላይ የተገለጸው ሰንደቅ አላማ የማቃጠል ድርጊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸመ አለመሆኑን አረጋግጧል።  

የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ሲቃጠል የሚያሳየውን ፎቶ እ.አ.አ ፌብርዋሪ 15/2019 ዓ.ም በአሶሸትድ ፕሬስ (AP)  የተሰራጨ ሲሆን ድርጊቱ የተፈጸመው ከካርቢያን ደሴቶች አንዷ በሆነችው ሀይቲ ነው። ሰንደቅ አላማውን ያቃጠለው ግለሰብ ብሮንሰን እንደሚባል የተጠቀሰ ሲሆን በአሜሪካ መንግስት ይደገፋል የሚባለውን የሃይቲ ፕሬዝደንት ጆቬናል ሞይስ ከስልጣን ይለቅ ዘንድ ለመጠየቅ ሰልፍ ከወጡ ወጣቶች አንዱ ነበር። 

ሀሰተኛና እና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የተነካኩና ከኣአውድ ውጭ ጥቅም ላይ የዋሉ ምስሎችን ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ይደገፉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::