የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተነስቷል?

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር (Ethiopia Insider) ከደቂቃዎች በፊት ‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ተወሰነ” በሚል ርዕስ ዜና በፌስቡክ ገጹ አሰራጭቷል።

ይሁን እንጂ ይህ ዜና የሚኒስትሮች ም/ቤት ለ6 ወራት የታወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር ዉሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን እንጂ የም/ቤቱ ዉሳኔ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ መጽደቅ እንዳለበት አልጠቀሰም።

ይህም ዜናዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚኒስትሮች ም/ቤት ዉሳኔ ብቻ እንደሚነሳ የሚያመለክት እንዲሆን አድርጎታል።

የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ያወጣዉ መግለጫ እንደሚያመለክተዉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጁ ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ተወያይቶ በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::