የዋልታ የፌስቡክ ገፅ በክሪፕቶ ከረንሲ ጠላፊዎች እጅ እንደገባ የሚፃፉት ኮዶች እንደሚያመላክቱ አንድ የዘርፉ ባለሙያ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን አሳውቋል!

እዚህ ስክሪንሾት ላይ የሚታየውን ፅሁፍ ያብራራልን የአክስዮን እና ክሪፕቶ ከረንሲ የሚገበያይ ነጋዴ የሆነው አብነት ተፈራ ነው። እንዲህ ብሎ ያብራራዋል: “እየጠየቁ ያሉት የክሪፕቶ ከረንሲ ቲተር (Tether) ነው። ቴተር ማለት ወደ አሜሪካ ዶላር የሚመነዘር እና የሚተመን መጠን ያለው ሲሆን ስሌቱም 1 $. 5000 USDT = 5000$ ነው።”

አክሎም “በስተመጨረሻ የሚታየው ረጅም ቁጥር ደግሞ ኤተሪየም ዋሌት (Ethereum wallet) አድራሻ ነው፣ በህግ አስከባሪዎች እንዳይታወቁ ደግሞ አድራሻውን እየቁያየሩት ይገኛል” ይላል ባለሙያው።

ገፁን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ጠላፊዎች የገፁን አድራሻ የቀየሩት ሲሆን የተለያዩ መልዕክቶችንም እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮቹ ይህን አውቀው የሚለጠፈው መልዕክት በጠላፊዎች እንደሆነ እንዲገነዘቡ ያሳውቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::