የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የዶክተር ይልቃል ከፋለን ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካውንቶች መኖራቸውን ተመልክተናል! 

ከአካውንቶቹ መካከል እ.አ.አ መስከረም 2021 ዓ.ም የተከፈተና ‘Dr Yilkal Kefale Asres’ የሚል መጠሪያ ያለው ይገኝበታል፣ አካውንቱ በአሁኑ ሰዐት ከ1,889 በላይ ተከታዮች  አሉት። 

ይህ የትዊተር አካውንት በተለይ ባለፉት ጥቂት ቀናት በርካታ መልዕክቶችን ሲያጋራ የተመለከትን ሲሆን በዚህም በመቶዎች የሚቆጠር ግብረመልስ ከተከታዮቹ እንደሚያገኝ አስተውለናል። 

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ይህ የትዊተር አካውንት ሀሠተኛ መሆኑን እና የሚያጋራቸው መልዕክቶችም የፕሬዝደንቱ አለመሆናቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል። 

የዶክተር ይልቃል ከፋለ ትክክለኛ የትዊተር አካውንት በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የተያያዘው መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ በፊት አሳውቆ ነበር: https://twitter.com/AserseKefale?t=8S3vHxY_DA6NxOhQ1A4bOw&s=09 

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የዘወትር መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::