በማዕድን ሚንስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ስም የተከፈተና ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የተዊተር አካዉንት የተለያዩ መረጃዎችን እያጋራ ይገኛል!

ከነዚሀም መካከል በትላንትናዉ እለት በአፋር ከልል ድፍድፍ ነዳጅ ቁፋሮና ማዉጣት ስራ መጀመሩንና የነዳጅ ዋጋም ከዛሬ ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ፅፏል። በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ተጠቃሚዎችም መረጃዉን ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ይህን ትዊተር አካዉንት በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ኢንጂነር ታከለ ኡማን መረጃ የጠየቀ ሲሆን አካዉንቱ የርሳቸዉ እንዳልሆነ አረጋግጠናል።

ሚንስትሩ ትዊተር “አካዉንቴ የተረጋገጠ (verified) ነዉ” ሲሉ ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል። የሚንስትሩ የተረጋገጠዉ ትዊተር አካዉንትም ከ480 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ነዉ።

የትክክለኛው አካውንት ሊንክ: https://twitter.com/TakeleUma?t=B8r0TqnfHGaY0E1etCEz7w&s=09

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::