ይህ ከ669,000 በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው!

በጋዜጠኛ እና ቶክ ሾው አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን ስም እና የቤተሰብ ምስል የተከፈተና ከ669 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ እንዳለ ተመልክተናል።

ገፁ የዛሬ ስምንት አመት ገደማ የተከፈተ ሲሆን በርካታ አስተዳዳሪዎች (Admins) እንዳሉት ይታያል። በተጨማሪም “Daily Addis”፣ “Daily Feta”፣ እና “ETHIOCOM.NET” ከተባሉ የዩትዩብ ቻናሎች እና ድረ-ገፆች ላይ የተለያዩ ቪድዮዎችን እያጋራ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ቼክ የገፁን ትክክለኛነት ለማጣራት ሰይፉን አናግሮ የነበረ ሲሆን የርሱ እንዳልሆነ እና የሚተላለፉት መልእክቶችም የእርሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::