“ዛሬ ሲኤንኤን ለዜና ግብአትነት የተጠቀመበት የትዊተር አካውንትም ሆነ በአካውንቱ ላይ የሰፈረው መልዕክት የኔ አይደለም”— ፕ/ር መረራ ጉዲና ለኢትዮጵያ ቼክ 

ሲኤንኤን (CNN) ዛሬ ‘Ethiopians head to the polls amid conflict and a raging humanitarian crisis’ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ረዘም ያለ ጽሁፍ አስነቧል። 

ሲኤንኤን ለጽሁፉ በግብአትነት ከተጠቀመባቸው መረጃዎች መካከል የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ስምና ምስል በጠቀም በተከፈተ የትዊተር አካውንት ላይ የተለጠፉ ትዊቶች ይገኙባቸዋል። 

ፕሮፌሰር መረራ ዛሬ ሲኤንኤን ለዜና ግብአትነት የተጠቀመበት የትዊተር አካውንትም ሆነ በአካውንቱ ላይ የሰፈረው መልዕክት የእርሳቸው አለመሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቀዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ይህ የትዊተር አካውንት የፕሮፌሰር መረራ አለመሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ሲኤንኤን (CNN) ዜናው ላይ ማስተካከያ አድርጓል! 

ሲኤንኤን (CNN) ዛሬ ‘Ethiopians head to the polls amid conflict and a raging humanitarian crisis’ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ረዘም ያለ ጽሁፍ አስነብቦ ነበር። 

ሲኤንኤን ለጽሁፉ በግብአትነት ከተጠቀመባቸው መረጃዎች መካከል የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ስምና ምስል በጠቀም በተከፈተ የትዊተር አካውንት ላይ የተለጠፉ ትዊቶች ይገኙበት ነበር። 

ፕሮፌሰር መረራ ዛሬ ሲኤንኤን ለዜና ግብአትነት የተጠቀመበት የትዊተር አካውንትም ሆነ በአካውንቱ ላይ የሰፈረው መልዕክት የእርሳቸው አለመሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቀዋል፣ ኢትዮጵያ ቼክም ይህን ዜና ዛሬ አስነብቦ ነበር። ይህን ተከትሎ የሚድያ ተቋሙ “incorrectly attributed” ያለውን የፕሮፌሰሩን ንግግር አርሟል።  

ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ይህ የትዊተር አካውንት የፕሮፌሰር መረራ አለመሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::