በአዲስ አበባ የሚገኙ ሚዲያዎች ነገ ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ተከለከሉ በሚል ዘ-ሐበሻ ያሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል! 

ኢትዮጵያ ቼክ የተወሰኑ ሚድያዎችን በዚህ ዙርያ ያናገረ ሲሆን ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ተናግረዋል።  

መግለጫው እንዲህ ይቀርባል: 

“የአዲስ አበባ ፖሊስ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር በገባበት እና የውጪ  እና ውስጥ  ሀገር ሚዲያዎች ፍቃድ አግኝተው የምርጫውን ሂደት እየዘገቡ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሚዲያ አካላት ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ተከለከሉ የሚል ሀሰተኛ መረጃ በዘ-ሐበሻ መለቀቁ አግባብነት የሌለው መሆኑን  ህብረተሰቡም  ሆነ መገናኛ ብዙኃን እንዲገነዘቡት መልእክቱን እያስተላፈ መሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ከህገ-ወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ  እና የኮሚሽኑን ገፅታ ይሁን በህብረተሰቡ ሰላምና ፀጥታ ላይ አሉታዊ ጫና የሚየሳድሩ ሀሰተኛና የተዛባ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡”

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::