“የ2014 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መስጫ ቀን አልተቆረጠም”— የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በተያዘዉ የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች “የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከግንቦት 22 – 25/ 2014 ዓ.ም ይሰጣል” የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ የገኛል። መረጃዉ በተማሪዎች ዘንድ ግርታን እየፈጠረ እንደሆነም ተመልክተናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑትን አቶ ቤከማ ስለሺ አናግሯል።

እርሳቸዉም “የ2014 /ፈተና/ መቼ እንደሚሰጥ አልታወቀም። ቀኑ አልተቆረጠም፤ ስለ ፈተናዉ ቀንም የተባለ ነገር የለም” ብለዋል። በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ያለዉ (ፈተናዉ ከግንቦት 22 – 25/ 2014 ዓ.ም ይሰጣል) የሚለዉ መረጃም በተቋሙ እዉቅና እንደሌለዉ ነግረዉናል።

“ፈተና የሚሰጥበት ቀን ሲቆረጥና ሲታወቅ በሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል” ብዋል አቶ ቤከማ ስለሺ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::