የሶማሌ ክልል ወቅታዊ ሁኔታና እየተጋሩ ስላሉ አሳሳች መረጃዎች!

ከትላንት ጀምሮ “የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሃመድ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገባቸዉ” የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

አብዛኞቹ መረጃዎችም አዲስ ስታንዳርድን እንደ ምንጭነት ሲጠቅሱም ተመልክተናል። ለምሳሌ ያህል ‘EthioMereja.net’ የተባለ የፌስቡክ ገጽ “ አዲስ ስታንዳርድ በዛሬው እለት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እንደተደረገባቸው እና ፀረ ሰላም ሀይሎች ክልሉን ለማወክ እና ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጋቸውን ዘግቧል” በማለት ጽፏል።

የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባወጣዉ መግለጫ በክልሉ ስላለዉ የድርቅ አደጋ፤ ድርቁን ለመቋቋም እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እንዲሁም ስለ ክልሉ ሰላም ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የክልሉ መንግስት ክልሉን የጦር አውድማ ለማድረግና ሰላምን ለማወክ ሴራ እየሸረቡ ከሚገኙ አካላት እና በድጋሚ ወደ መንግሥት መዋቅር ለመመለስ በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እየታገለ እንደሆነ በመግለጫዉ ተጽፏል።

በተጨማሪም የክልሉን ሰላም ለማወክና ስልጣንን በሀይል ለመያዝ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ አካላት እንዳሉም የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ይናገራል።

ነገር ግን በክልሉ ፕሬዝዳንት ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን የሚጠቅስ መረጃ በመግለጫዉ ላይ የለም፣ አዲስ ስታንዳርድ ያወጣው ዜናም ይህን እንደማይገልፅ ተመልክተናል።

በተጨማሪም ቢሮው የክልሉ መዲና ጅግጅጋን አስመልክቶ ከሰአታት በፊት ባወጣዉ መግለጫ ከተማዉ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መፈንቅለ መንግሥት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ግልጿል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::