በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌግራም አገልግሎት አሁን መስራት ጀምሯል!

ኢትዮጵያ ቼክ ማረጋገጥ እንደቻለው የቴሌግራም መተግበርያ በመላው ኢትዮጵያ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መስራት አቁሞ ነበር።

በበርካቶች ዘንድ መልእክት ለመለዋወጫ ተመራጭ እየሆነ የመጣው ቴሌግራም ለምን መስራት እንዳቆመ በግልፅ ባይታወቅም ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያያዞ አንዳንድ የቴሌግራም ግሩፖች ላይ ህገወጥ ፅሁፎች ሲንሸራሸሩ እንደነበር ቅሬታዎች ሲቀርቡ ነበር።

ከሚመለከተው አካል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ እያረግን የነበረ ሲሆን መልስ ማግኘት አልቻልንም። ዛሬ ቀትር ላይ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ቴሌግራም ዳግም መስራት ጀምሯል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::